ቀጥታ፡

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ለፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤መስከረም 4/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ለፍጻሜ አልፋለች።

አትሌት ፍሬወይኒ በምድብ አንድ ባደረገችው ውድድር 4 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ ከ03 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥታለች።

ማጣሪያው በሁለት ምድቦች ተከፍሎ የተደረገ ሲሆን የምድቡ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል።

አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ የፍጻሜ ውድድሯን ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ከ5 ላይ ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም