ቀጥታ፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዛሬ ያለንን ጥበብና ብልኃት የሚቃኝ፤ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ገድል ነው-ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤መስከረም 4/2017 (ኢዜአ)፡-ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዛሬ ያለንን ጥበብና ብልኃት የሚቃኝ እንዲሁም ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ ገለጹ።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ ''ኢትዮጵያ ችላለች'' በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ትናንት የነበረውን የኢትዮጵያውያን የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዛሬ ያለንን ጥበብና ብልኃት የሚቃኝ እንዲሁም ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ስለሆነ አሳንሰን ልናየው አንችልም ብለዋል።

ኢትየጵያውያን አርቀው ያስባሉ፤ይመራመራሉ፤ ይፈጽማሉ፤ደግሞም ሠርተው ያሳያሉ ሲሉም ገልጸዋል ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም