ብሬንትፎርድ እና ቼልሲ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ብሬንትፎርድ እና ቼልሲ ነጥብ ተጋርተዋል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ብሬንትፎርድ እና ቼልሲ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በጂቴክ ኮሙዩኒቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኬቨን ሻድ በ35ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ብሬንትፎርድ መሪ ሆኗል።
ኮል ፓልመር በ61ኛው እና ሞሰስ ካሲዬዶ በ85ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፏቸው ጎሎች ቼልሲ መሪነቱን ወስዷል።
ተቀይሮ የገባው ፋቢዮ ካርቫሊዮ በ94ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋት ግብ ብሬንትፎርድ አንድ ነጥብ አግኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ብሬንትፎርድ በአራት ነጥብ 12ኛ፣ ቼልሲ በስምንት ነጥብ 5ኛ ደረጃን ይዘዋል።