ቀጥታ፡

አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርቲን ዙቢሜንዲ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቪክቶር ዮኮሬሽ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በዘጠኝ ነጥብ የሊጉን መሪነት በጊዜያዊነት ከሊቨርፑል ተረክቧል።

ኖቲንግሃም ፎረስት በአራት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም