ቀጥታ፡

በ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ የተሳተፉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በተካሄደው የ3000 ሜትር ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለ እና ሳሙኤል ፍሬው ለፍጻሜ አልፈዋል።


 

የማጣሪያ ውድድሩ በሶስት ምድቦች ተከፍሎ የተከናወነ ሲሆን ከየምድቡ ከአንድ እስከ አምስት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።


 

የፍጻሜ ውድድሩ ሰኞ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም  ከቀኑ 9 ሰዓት ከ55 ላይ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም