አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2018 (ኢዜአ)፦ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፍ ችላለች።
አትሌት ፍሬወይኒ በምድብ ሶስት ባደረገችው ውድድር 4 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ ከ23 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥታለች።
በምድብ አንድ የተወዳደረችው አትሌት ሳሮን በርሄ 4 ደቂቃ ከ7 ሴኮንድ ከ6 ማይክሮ ሴኮንድ ዘጠነኛ በመውጣት ለግማሽ ፍጻሜ አላለፈችም።
ማጣሪያው በአራት ምድቦች ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን ከየምድቡ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ለፍጻሜ ለማለፍ ነገ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ5 ላይ ውድድሯን ታደርጋለች።