ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 3/2018 (ኢዜአ)፦አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኘች።

ኬንያዊቷ አትሌት ቢትሪስ ቺቤት የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ ጣልያናዊቷ ናዲያ ባቶሌቲ ሁለተኛ ወጥታለች።

እጅጋየሁ ታዬ 5ኛ፣ ፎትየን ተስፋይ 8ኛ እና ፅጌ ገብረሰላማ 22ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በጃፓን ቶኪዮ የሚካሄደው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ መጀመሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም