የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፈተ
አዲስ አበባ፤መስከረም 3/2018 (ኢዜአ)፦ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ መመረቃቸው ይታወቃል።
የግድቡን መጠናቀቅ በማስመልከትም ዛሬ በአዲስ አበባ የግድቡን የግንባታ ሂደት፣ የሕዝብ ተሳትፎና ስኬቱን የሚያሳይ የፎቶና የስዕል አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተከፍቷል።
በስዕል አውደ ርዕዩ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
"በህብረት ችለን አሳይተናል" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይትም እየተካሄደ ይገኛል።