ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህልማችንን በጋራ ያሳካንበት ፕሮጀክት ነው - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህልማችንን በጋራ ያሳካንበት ፕሮጀክት ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2018(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህልማችንን በጋራ ያሳካንበት ፕሮጀክት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የማስ እስፖርት ተካሂዷል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ወጣቶች የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
አቶ ጃንጥራር አባይ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህልማችንን በጋራ ያሳካንበት ፕሮጀክት ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከሀብታም እስከ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ድረስ በመረባረብ በጋራ ያሳኩት ድል መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያን የላብ የደም እና የእንባ መስዋዕትነት የከፈሉበት መሆኑን ገልጸው አሁንም መስዋእት እየሆንን ለሃገራችን ዘላቂ ልማት በጋራ እንቆማለን ብለዋል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪችም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕሴው ግድብ መመረቅ የተሰማቸውን ደስታ በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል።