ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ2018 አዲስ ዓመትን በሚኖሩባቸው አገራት አከበሩ

አዲስ አበባ፤መስከረም 1/2018 (ኢዜአ)፦በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አክብረዋል።

በዓሉ ከጳጉሜን ቀናት ጋር በማስተሳሰር በየአገራቱ በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ተከብሯል።

ዳያስፖራው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት የተሰማውን ደስታ በሁነቶቹ ላይ በስፋት አንጸባርቋል።

የዳያስፖራው ማህበረሰብ በአዲስ ዓመት አከባበር ላይ ለሀገሩ ልማት እና እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

አሜሪካ፣ፈረንሳይ፣ቤልጅየም፣እንግሊዝ፣ሩሲያ፣ ኩዌት፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ህንድ፣ ፓኪስታን ሩዋንዳ እና ጅቡቲ በዓሉ ከተከበረባቸው አገራት መካከል ይገኙበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም