ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2017(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ዛሬ ጠዋት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኬር ማያርድትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

አክለውም፥ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ትብብራችንን ለማጠናከር እና የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮችንም ተመልክተናል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም