ቀጥታ፡

ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 5 /2017 (ኢዜአ)፦ትናንትን በመጠቀምና በማረም፣ ዛሬ ላይ ተግተን በመሥራት፣ ነገን እጅግ የተሻለ ለማድረግ ተነሥተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነገው ቀንን አስመልክቶ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ረገድ ባስተላለፉት መልዕክት በአናሎግ ዘመን የነበሩ ችግሮች በዲጂታል ዘመን አይደገሙም ብለዋል።


 

ነገ “ዲጂታል ኢትዮጵያ” ፕሮጀክት ከመሆን አልፎ ባህል እንደሚሆን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ጠቁመዋል፡፡

ንግድ እና አገልግሎታችንን በማቀላጠፍ፣ መረጃዎቻችንን ተደራሽ በማድረግ፣ አንድ ሰው አንድ እንዲሆን በማስቻል፣ የፋይናንስ ሥርዓታችንን ይበልጥ ተደራሽ ቀልጣፋ እንዲሆን በማድረግ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን በየአቅጣጫው በማስፋፋት፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ እንዲሳካ የሁላችንን ጥረትና ትኩረት እንደሚፈልግ ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም