በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ልደታ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ልደታ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተደርገዋል።
ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል። ቢታኒያ አስተረፍ፣ መስታወት አመሉ እና ስመኝ ምህረቱ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሌላኛው መርሃ ግብር ልደታ ክፍለ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ቃልኪዳን ጥላሁን በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ይታገሱ ተገኝወርቅ ቀሪዋን ጎል አስቆጥራለች።
ይዲዲያ አጫ ለድሬዳዋ ከተማ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝታለች።
ይርጋጨፌ ቡና እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።