የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሴራሊዮን ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሴራሊዮን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር ባደረገው የምድብ አንድ ስምንተኛ ጨዋታ 2 ለ 0 አሸንፏል።
ላይቤሪያ ሞኖሮቪያ የሚገኘው ሳሙኤል ካንዮን ዶ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ኢብራሂም ካማራ በ37ኛው ደቂቃ እና አልሃሳን ኮሮማ በ96ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በስድስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ሴራሊዮን በ12 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።