ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካውያን ፕሮጀክት ነው - የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማርጌሌ - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካውያን ፕሮጀክት ነው - የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማርጌሌ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካውያን ፕሮጀክት ነው ሲሉ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማርጌሌ ገለጹ።
በኢትዮጵያውያን ገንዘብ፣ የላብ እና የደም ጠብታ እውን የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በይፋ ተመርቋል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማርጌሌ፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ ነው ብለዋል።
ግድቡ የዓለምን ሕዝብ ያስደነቀ የአፍሪካ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል።
የግድቡ መሳካት ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ድል መሆኑን በማንሳት፥ ለዚህም የከበረ አድናቆት አለን ነው ያሉት በንግግራቸው።
የግድቡ ግንባታ በመጠናቀቁ ሁላችንም ደስ ብሎናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ የግድቡ ግንባታ በኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ለፍጻሜ መብቃቱ እጅግ የተለየ አድናቆት የሚቸረው ነው ብለዋል።