ኢትዮጵያ የህዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ ትጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የህዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ ትጀምራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 4/2017 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃን በይፋ ባበሰሩበት ወቅት የኢትዮጵያን ቀጣይ ሜጋ ፕሮጀክቶች ይፋ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ በድምሩ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት የሚፈስባቸው የአፍሪካን ልጆች ቀና የሚያደርጉ የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያሳኩ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን እናደርጋለን ነው ያሉት።
ከእነዚህ መካከል፡-
👉ኢትዮጵያ የሕዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ ትጀምራለች።
👉በአፍሪካ ግዙፍ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ይጀመራል።
👉በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካ ይመረቃል።
👉በተመሳሳይ ቀን ከመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካ ከ10 እጥፍ በላይ ከፍ ያለ የጋዝ ምርት ሥራ ይጀምራል።
👉ነዳጅ የማውጣት የዘመናት ፍላጎታችንን እውን የሚያደርግ የነዳጅ ማጣሪያ በአንድ ወር ውስጥ ሥራ ይጀምራል።
👉በተመሳሳይ ሰሞን ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ይጀመራል።
👉በሚቀጥሉት አምስት ስድስት ዓመታት ቢያንስ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ለኢትዮጵያውያን ይገነባሉ።
ኢትዮጵያውያን ከፊታችን ለሚጠብቀን ከባድ ስራ ታጥቀን በመነሳት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማፋጠን በጋራ አብረን እንድንቆም ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።