በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነት በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ - ኢዜአ አማርኛ
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነት በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነትና ትብብር በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።
በኢትዮጵያዊያን ገንዘብ፣ የላብ እና የደም ጠብታ እውን የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቋል።
በምረቃው ላይ የተገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላልፈዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለምረቃ በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ በግድቡ ግንባታ የታየው አንድነትና ትብብር በሌሎች ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።