ለጋራ ዕድገታችን ቀጣናዊ ትብብር ወሳኝ ነው-ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ - ኢዜአ አማርኛ
ለጋራ ዕድገታችን ቀጣናዊ ትብብር ወሳኝ ነው-ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 4/2017 (ኢዜአ)፡- ለጋራ ዕድገታችን እንደ ጎረቤት ሀገራት ሁላችንም በትብብር መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ታላቁን የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ መርቀዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እንዳሉት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተመርቆ በመጠናቀቁ ኢትዮጵያውያንን እንኳን ደስአላችሁ ብለዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በመገኘታቸው መደሰታቸውን ጠቅሰው፥የግድቡ ተገንብቶ መመረቅ ለቀጣናው ኩራት መሆኑንም አንስተዋል።
የግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ላለው የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።
ፕሮጀክቱ ከአንድ ግድብነት ያለፈ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሶማሊያ ፍላጎት ግልጽ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በትብብር መልማትና ማደግ መሆኑን አሳውቀዋል።
ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያከናወነችው ሥራ ትልቅ ታሪክ መሆኑን በመግለጽ፥ለሀገራቸው የሚጠቅም ተነሳሽነት መሆኑንም አስረድተዋል።