የአባይ የዘመናት ቁጭት አብቅቶ ለስኬት በመብቃታችን ደስታችን ወደር የለውም- የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
የአባይ የዘመናት ቁጭት አብቅቶ ለስኬት በመብቃታችን ደስታችን ወደር የለውም- የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች

ወላይታ ሶዶ፤ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦የአባይ የዘመናት ቁጭት አብቅቶ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ለስኬት በመብቃታችን ደስታችን ወደር የለውም ሲሉ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን ተከትሎ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች በተለያዩ ትእይንቶች ደስታቸውን ገልጸዋል።
በጋራ ጥረታችን፣ በጥሪታችንና በጉልበታችን ግዙፍ ፕሮጀክት ገንብተን በማጠናቀቅ ለምርቃት በመብቃቱ የሁላችንም ስኬትና እለቱም የደስታ ቀን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በዚህ የግንባታ ሂደት መንግስት ያሳየው ቁርጠኝነትና በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለነበራቸው የላቀ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የግድቡን ምርቃት በማስመልከት የወላይታ ሶዶ ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎቹ በጎዳናዎች በመዘዋወር ደስታቸውን ገልጸዋል።
የአባይ የዘመናት ቁጭት አብቅቶ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ለስኬት በመብቃታችን ደስታችን ወደር የለውም ሲሉም ተናግረዋል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የህዝባዊ የደስታ መግለጫ ላይ የወላይታ ዞንና ከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና በርካታ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።