ቀጥታ፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ ስኬታችን ማሳያ ነው

ሰመራ፤ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጋራ መጠሪያችንና የስኬታችን ማሳያ ነው ሲሉ የሰመራና ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምረቃ መብቃቱን አስመልክተው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የሰመራና ሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች "ለዓመታት የጠበቅነው የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና እውን መሆን ደስታችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል" ብለዋል።

ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ጀማል መሐመድ እንዳሉት ፕሮጀክቱ አገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችው የብልፅግና ጉዞ መዳረሻን ያሳየ እና የጋራ መጠሪያችን ነው።


 

ግድቡ አገራችን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለመሆን የምታደርገውን ጥረት አጉልቶ ያሳየ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊያን አንድነታችን የጎለበተበትና ወደ ከፍታ የምናደርገውን ግስጋሴ ያፋጠነ ፕሮጀክት ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው፤  የወደፊቱን የብርሃን ጊዜ ያመላከተ በመሆኑ ደስ ብሎኛል ብለዋል።

ግድቡ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በማየቴ ደስታዬ ወደር የለውም ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ ነዋሪ ሃዋ አሎ ናቸው።


 

"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን መጠናቀቅ በጉጉትና በተስፋ ስንጠብቀው ነበር" ያሉት ደግሞ አቶ አብዱ ሐሰን ናቸው።

ላለፉት ዓመታት ከደሞዛቸው ቦንድ በመግዛት የተሳተፉ መሆኑን ገልፀው ይኸውም የላባችን ውጤት ነው ሲሉ አስረድተዋል።


 

አቶ ጀማል አብዱ በበኩላቸው ያበረከትኩት ትንሽ አስተዋፅኦ ለውጤት በመብቃቱ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም