ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ታሪክ ሆኖ የሚቀጥል ገድል ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ታሪክ ሆኖ የሚቀጥል ገድል ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ታሪክ ሆኖ የሚቀጥል ገድል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መርቀዋል።
በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም፤ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለጥቁር ሕዝቦች በሙሉ ታሪክ ሆኖ የሚቀጥል ታላቅ ገድል መሆኑን ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በአካል ካልተመለከቱ በቀር በልኩ ማወቅ ስለማይቻል፤ ይህ ትውልድ የሠራውን ገድል እየመጣ እንዲያይም ጋብዘዋል።
በተጨማሪም የጥቁሮች ኩራት ስለሆነ ሌሎች ጥቁር ሕዝቦችም እንደምንችል ማሳያ በመሆኑ እንዲጎበኙትም እንዲሁ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትናንት ቁጭት ማሰሪያ፤ የመጭው ተስፋ ማብሠሪያ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።