ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን ንጋት ሐይቅ ማሳያ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን ንጋት ሐይቅ ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን መርቀዋል።

በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ወንድሞቿን ለመጉዳት እንዳልገነባችውና የሚገባቸውን እንደማታስቀር አረጋግጠዋል።

በቀጣይ በምንሠራቸው በርካታ ሥራዎች በትብብር ተያይዘን እንቀጥል ብለዋል።


 

በሌላ በኩል በሕዳሴው ግድብ ላይ ያለው የኢትዮጵያን ጨለማ መንጋት የሚያበሥረው ንጋት ሐይቅ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በጉባ ላይ ዳግም ዓድዋ መሠራቱን ገልጸው፤ የኢትዮጵያ የልመናና የቁጭት ጊዜ አልፏል ነው ያሉት።

የኢትየጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑንም ንጋት ሐይቅ ማሳያ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ተረጂነቷ ተጠናቅቋል፤ በቀጣይም ረጂ ትሆናለች ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም