ቀጥታ፡

የህዳሴ ግድብ ምረቃን ተከትሎ  የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው

ሀዋሳ ፤ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ምረቃን ተከትሎ  የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

የከተማው ነዋሪዎች በጎዳና ላይ በመውጣትና በመዘዋወር እንዲሁም በተሽከርካሪ ትርኢትና በሌሎች ሁነቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው።


 

የተሽከርካሪ ትርኢቱ ከሀዋሳ ከሼል አደባባይ የጀመረ ሲሆን የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ የተካሄዱ ጥረቶችና ስኬቱን የሚያወሱ  የጎዳና ላይ ትርኢቶች  በነዋሪዎች እየቀረቡ ነው።


 

በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ታምሩ ታፌን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም