ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን መረቁ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ተገኝተዋል።


 

በተጨማሪም ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ፤የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል፡፡


 

እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።


 

እንዲሁም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አኅጉር አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ነው የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የተከናወነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም