ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዲስ ተመራጮች የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዲስ ተመራጮች በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ናቸው።

በጉብኝቱኝ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ አመራሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የምክር ቤቱ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችም ተገኝተዋል።

በዚህም አዲሱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት እና አመራሮች የሳይንስ ሙዝየምን የጎበኙ ሲሆን በቀጣይም በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ ማጠቃለያ መርኃ ግብር በትላንትናው እለት በአንዋር መስጅድ መካሄዱ ይታወሳል።

በምርጫው ጠቅላይ ምክር ቤቱን ለመጪዎቹ አምስት አመታት የሚመሩ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንትና ጸሐፊን ጨምሮ የስራ አስፈጻሚዎች ተመርጠዋል።

በዚህም ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ፕሬዝዳንት፣ ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ሼህ ጁነይድ ሀምዛ እና ሼህ ሀሚድ ሙሳ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም