ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ግሬናዳ በትብብር ለመሥራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከግሬናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ አንድል ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ውይይቱ የተደረገው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው ሁለተኛው የአፍሪካ-ካሪቢያን ማኀበረሰብ ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ነው።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ላይ፤ በአፍሪካና በካሪቢያን መካከል ያለውን ታሪካዊ ትስስር ወደ ተጨባጭ ትብብር መቀየር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያና ግሬናዳ በቀጣይ፤ በጤና፣ ዲኘሎማሲ፣ በሠለጠነ የሰው ኃይል ስምሪት እና በአቪዬሽን መስኮች ትብብር ለማድረግ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም