ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በሕዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ ተጠናቋል

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በሕዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ በመጠናቀቁ ሰላም ሚኒስቴር ለዕምነቱ ተከታዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መረጃ፤ ሕዝበ ሙስሊሙ መሪውን በድምፁ በመምረጥ ተቋሙን በነፃነት ለመምራት ለዘመናት ሲታገል መቆየቱን አስታውሷል።

ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው መልካም ዕድል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዋጅ ሊቋቋም ችሏል ብሏል።


 

ሕዝበ ሙስሊሙ በነፃነት ለቀጣይ አምስት ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ መሪዎችን በነቃ ተሳትፎ፣ በብልኅነት፣ በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜትና ኃላፊነት፣ አካታችና የመላው ሕዝባችንን ሰላምና ሀገራዊ የአብሮነት መንፈስን በሚያጠናክር መልኩ በማጠናቀቁ ሚኒስቴሩ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

በየደረጃው ተቋሙን ለመምራት ኃላፊነትን ከተረከቡት የዕምነቱ አባቶች ጋር በቅርበት እንደሚሠራም ነው ያስታወቀው።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ፤ በሰላም፣በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጀመረውን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያለውን ተስፋ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም