ቀጥታ፡

ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 2/2017(ኢዜአ)፦ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆኖ በድጋሜ ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአንዋር መስጅድ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሰብሳቢ አብዱላዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የ2017 ምርጫ "ምርጫችን በመስጂዳችን" በሚል መሪ ሃሳብ ከነሐሴ 9 ቀን 2017 ጀምሮ ሲከናወን መቆየቱን ተናግረዋል።

ምርጫው አሳታፊ በሆነ መልኩ ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።


 

በምርጫው ጠቅላይ ምክር ቤቱን ለመጪዎቹ አምስት አመታት የሚመሩ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንትና ጸሐፊን ጨምሮ የስራ አስፈጻሚዎች መመረጣቸውን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ፕሬዝዳንት፣ ሼህ አብዱልከሪም በድረዲን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ሼህ ጁነይድ ሀምዛ እና ሼህ ሀሚድ ሙሳ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አስታውቀዋል።


 

እንዲሁም ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ ዋና ፀሀፊ በመሆን መመረጣቸውን ገልፀዋል።


 

ጠቅላይ ምክር ቤቱን ለቀጣይ አምስት አመታት እንዲመሩ የተመረጡ ከፍተኛ አመራሮች በታላቁ አንዋር መስጂድ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም