ቀጥታ፡

ለሀገራችን ብልፅግና በህብረት በመቆም በሁሉም መስክ ስኬትን እናስመዘግባለን

ቦንጋ፤ ጳጉሜን 2 /2017(ኢዜአ)፦በህብረ ብሔራዊ አንድነት ለሀገራችን ብልፅግና በህብረት ስንቆም በሁሉም መስክ ስኬትን እናስመዘግባለን ሲሉ በቦንጋ የህብር ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀ ፓናል ውይይት ተሳታፊዎች ገለፁ።

ጳጉሜን 2 የህብር ቀን "ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከ76 በላይ ብሔረሰቦች ህብረ-ብሔራዊ አንድነታቸውን ጠብቀው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗን ገልፀዋል። 


 

መንግስት ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር በርካታ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም ይህንኑ በማጠናከር ለጋራ ብልፅግና መቆም ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል። 

በብልፅግና ፓርቲ የካፋ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ  አቶ ታምሩ ታከለ፣ የህብር ቀንን ስናከብር ባለፉት ዓመታት አጋጥመውን የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን በፅናት በማለፍ በህብረትና በአንድነት ያስመዘግብናቸውን ድሎች በመዘከርና ለተሻለ ውጤት በመትጋት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። 

ሀገራዊ አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት አብሮነትን ማጠናከር፣ የትላንቱ ታሪካችንን ለነገ መማሪያ በማድረግ ለሀገር ግንባታ  በጋራ መቆም ይገባል ብለዋል። 


 

''አንድ ስንሆን የማንችለው ነገር የለም'' ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች በህብረ ብሔራዊ አንድነት ለሀገራችን ብልፅግና በህብረት ልንቆም ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም