ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ህብር የሚለው ቃል የሚገልፃት በአንድነት ያጌጠ ብዝሃነት ያላት አገር ናት 

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ህብር የሚለው ቃል የሚገልፃት በአንድነት ያጌጡ ብዝሃነት ያላቸው ብሄሮች ብሄረሰቦች ተሳስረው የሚኖርባት አገር ናት ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ገለፁ።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ ብዝሃ መልክ ያላት የብሄሮች ብሄረሰቦች አገር ናት።

በኢትዮጵያ ያሉ ብሄሮች ብሄረሰቦች የራሳቸው መገለጫ የሆነ ባህል፣ ቋንቋና አኗኗር ዘይቤ ያላቸው መሆናቸውን አንስተው፤ የተለያየ መልክዓ ምድርና አየር ፀባይ የታደለች አገር እንደሆነችም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የሃይማኖት ብዝሃነት ያላት ህብር የሚለው ቃል በርግጥም የሚገልፃት አገር መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በአንድነት ያጌጠ ብዝሃነት ያላትና ብዝሃነትን ከአንድነት ያስተሳሰሩ የውብ ህዝቦች አገር መሆኗንም ጠቁመዋል።

የራሳቸው መለያ ያላቸው ብሄሮች ብሄረሰቦች በአንድ አገረ መንግስት ጥላ ስር የኖሩ፣ የተሳሰሩባትና በእጅጉ የተጋመዱ ህዝቦች መሆኗንም ተናግረዋል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ከፍ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን አመልክተው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገሩ ጉዳይ እኩል ተሳትፎ እንዲኖረው መደላድል መፍጠር የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በህብር የተዋበ ብዝሃነትን ከአንድነት ያስተሳሰሩና የተጋመዱ ህዝቦች ያሉባት አገር መሆኗን ገልፀዋል። 

ብዝሃነት ለኢትዮጵያዊያን የአንድነት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ምንጭ፣ የቱሪዝምና ዲፕሎማሲ አቅም ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም