ቀጥታ፡

አንድነትና ወንድማማችነትን በማጠናከር ልማታችንን እናስቀጥላለን - ወይዘሮ ሀሊሞ ሀሰን 

ጅግጅጋ፤ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡-አንድነትና ወንድማማችነትን በማጠናከር ልማታችንን እናስቀጥላለን ሲሉ የሶማሌ ክልል ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀሊሞ ሀሰን ገለጹ። 

"ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥና ዐቅም ነው" በሚል መሪ ሃሳብ የህብር ቀን በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ነው።


 

በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ባለው የህብር ቀን የሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃለፊ አቶ መሀመድ አደን እና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የእግር ጉዞ ተካሄዷል።


 

በመርሃ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀሊሞ ሀሰን አንድነትና ወንድማማችነትን በማጠናከር ልማታችንን እናስቀጥላለን ብለዋል። 

መገናኛ ብዙሃን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ብዝሃነትና አንድነትን በሚያስቀጥሉ ተግባራት ላይ እየሰሩ ያሉትን ሥራ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም አሳስበዋል።

እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት ላይም በሕብረ-ብሔራዊነትና በአንድነት በክልሉ የተፈጠሩ የልማት፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ትሩፋቶችን የሚያሳይ ዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፍትህና የፀጥታ አካላት፣ ምሁራን እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ተወካዮች ተካፋይ ሆነዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም