ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ የመሪዎች ስብሰባ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ የመሪዎች ስብሰባ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡-ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ የመሪዎች ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአንጎላ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር ጃኦ ሎሬኔዞ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር የካሪቢያን ሀገራት ማህበረሰብ ዋና ጸሀፊ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ካርላ ባርነት ሞተሊን ጨምሮ የሌሎች የካሪቢያን ሀገራት መሪዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ "ለአፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትህን ለመሻት አህጉር ተሻጋሪ አጋርነት" የሚል መሪ ሀሳብ የያዘ ነው።
ጉባኤው የአፍሪካና ካሪቢያን ሀገራት በደቡብ ደቡብ የትብብር መንፈስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከርና የጋራ ድምፅ ለማሰማት መሰረት ለመሆን ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
አፍሪካ ከካረቢያን ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና ትብብር መቀየር ያስችላል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ በጉባኤው ላይ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው።