ህብረ ብሄራዊነታችንን አጠናክረን የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እውን እናደርጋለን - ኢዜአ አማርኛ
ህብረ ብሄራዊነታችንን አጠናክረን የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እውን እናደርጋለን
ሰመራ፤ጳጉሜን 2/2017 (ኢዜአ)፡- ህብረ ብሄራዊነታችንን አጠናክረን የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እውን እናደርጋለን ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአፋር ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የስፖርት፣ ባህልና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃሚድ ዱላ ተናገሩ።
"ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥና ዐቅም ነው" በሚል መሪ ሐሳብ የህብር ቀን በሰመራ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች በመከበር ላይ ነው።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የስፖርት፣ ባህልና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃሚድ ዱላ ህብረ ብሄራዊነትን በማጠናከር የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ እውን እናደርጋለን ብለዋል።
የጋራ ማንነቶችን በማጉላትና በልዩነታችን ውስጥ ያለውን አንድነት በማድመቅ ተምሳሌት የሆንበትን ገፅታችንን እናጠናክራለን ሲሉም ተናግረዋል።
አብሮነታችን ዘላቂነት እንዲኖረው በመከባበር ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል ያሉት ሃላፊው፤ ይኸም በአንጻሩ የምናልመውን ብልጽግናችንን እንድንጎናጸፍ ሃይል ይሆነናል ብለዋል።
በዚሁ ዕለት ስፖርታዊ ትዕይንትና የማዕድ ማጋራት መርሃግብር የተካሄደ ሲሆን የፓናል ውይይትና የደም ልገሳ መርሃ ግብርም ይካሄዳል።
በመርሐግብሩ የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡመር ኑሩን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሰመራ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።