በእድገትና ብልጽግና ጉዟችን የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩም በጽናት እየታለፉ በስኬት መንገድ እንደቀጠለ ነው- ከንቲባ ከደር ጁሃር - ኢዜአ አማርኛ
በእድገትና ብልጽግና ጉዟችን የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩም በጽናት እየታለፉ በስኬት መንገድ እንደቀጠለ ነው- ከንቲባ ከደር ጁሃር
ድሬዳዋ፣ ጳጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፡- በእድገትና ብልጽግና ጉዟችን የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩም በጽናት እየታለፉ በስኬት መንገድ እንደቀጠለ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከደር ጁሃር ገለጹ።
የጽናት ቀን "ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት ተከብሯል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ በእድገትና ብልጽግና ጉዟችን የተለያዩ ፈተናዎች ቢኖሩም በጽናት እየታለፉ በስኬት መንገድ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል።
ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በመጨረስ በዚህ ትውልድ አዲስ የብርሃን ታሪክ መፃፍ ስለመቻሉ አንስተው ሌሎች የስኬት ማሳያዎች እንዳሉም ተናግረዋል።
በመሆኑም የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የብልፅግና ጉዞ በማሳካት ለመጪው ትውልድ የምትመች ሀገር ለማስረከብ የትብብር ጥረታችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ፣ ለፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊነት አቶ አብዱልሰላም አህመድ፤ ሰላምን በማጽናት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የትብብር ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።