ዲስትሪክቱ በሆለታ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ዲስትሪክቱ በሆለታ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ
አምቦ፤ ነሐሴ 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት በሆለታ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።
የዲስትሪክቱ ዳይሬክተር ባይሳ ቦሶና፤ በባንኩ የተደረገው ድጋፍ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ወገኖች በዘመን መለወጫ በዓል ያለችግር እንዲያሳልፉ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
በድጋፉ ስነስርዓት ላይ እንደገለጹት ባንኩ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 210 የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የምግብ እህልና ዘይት በጥሬ ገንዘብ በድምሩ የ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
የሆለታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እሸቱ በቀለ፤ ባንኩ በዓልን መሰረት አድርጎ ለዜጎች ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።
የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖችም በባንኩ ለተደረገላቸው መልካም ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።