ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲሱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ መርቀው ከፈቱ - ኢዜአ አማርኛ
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አዲሱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፦የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በኮዬ ፈጬ ያስገነባውን አዲሱን የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ መርቀው ከፍተዋል።
ጠቅላይ መምሪያውን በበላይነት በመቆጣጠር በባለቤትነት ያሰራው የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሲሆን ግንባታውን ያከናወነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን መሆኑም ተገልጿል።
ጠቅላይ መምሪያው ዘመናዊ የአይሲቲ ቴክኖሎጂን ጨምሮ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የነዳጅ ዲፖ፣ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የጋራዥ ወርክ ሾፕ እና መሰል ግንባታዎችን አካትቷል።
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ሥራንም ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡