ቀጥታ፡

የአንጎላው ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ጆኦ ሎሬንቾ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2017 (ኢዜአ)፡- የአንጎላው ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ጆኦ ሎሬንቾ በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ እና በአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።


 

ፕሬዚዳንት ጆኦ ሎሬንቾ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

በተመሳሳይ የአንጎላው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴቴ አንቶኒዮ በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን የማህበረሰብ እና የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ሲገቡ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም