ቀጥታ፡

ፀንተን በጋራ በመተባበር የክልላችንን ሰላምና ልማት አጠናክረን እንቀጥላለን - የሶማሌ ክልል

ጅግጅጋ ፤ ጰጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፡- ፀንተን በጋራ በመተባበር  ለክልላችን  ሰላም ግንባታ ፣ልማትና እድገት  ይበልጥ  ጠንክረን እንሰራለን   ሲሉ  የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ  ሁሴን ቃስን(ዶ/ር) ገለጹ።  

ጳጉሜን 1 የፅናት ቀን "ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሀሳብ  በጅግጅጋ ከተማ  በተለያየ ዝግጅት  ተከብሯል። 


 

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ  ሁሴን ቃስን (ዶ/ር) ፤ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ፤ ለሀገራችን መፅናትና ሰላም መስፈን መስዋዕትነት  የከፈሉ ጀግኖችን  በማስታወስ የኢትዮጵያን  ልማትና እደገት ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል። 

ፀንተን በጋራ በመተባበር  ለክልላችን   ብሎም ለሀገራችን  ሰላም ግንባታ ፣ ልማትና እድገት ይበልጥ  ጠንክረን እንሰራለን   ብለዋል።


 

ገራድ ኩልሚዩ ገራድ መሀመድ በበኩላቸዉ፤  የሀገራችን ጽናት የሚያመላክቱ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ተከናዉኗል ሲሉ ገልጸዋል።

አክለዉም የፅናት አርማ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ  ሕዳሴ ግድብ እዚህ ደረጃ መድረስ አኩሪ መሆኑንም  አንስተዋል። 

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም