ቀጥታ፡

በለውጡ ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም በፅናት በማለፍ አስደናቂ ስኬቶች ተመዝግበዋል

ሃዋሳ ፤ጳጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፦በለውጡ ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም በፅናት በማለፍ ዘርፈ ብዙ አስደናቂ ስኬቶችን አስመዝግበናል ሲሉ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ ገለጹ።

ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን "ፅኑ መሰረት ብርቱ ሀገር" በሚል መሪ ሃሳብ በሲዳማ ክልል ተከብሯል።


 

በመርሃ-ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ፤በለውጡ ዓመታት ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም በፅናት በማለፍ ዘርፈ ብዙ አስደናቂ ስኬቶችን አስመዝግበናል ብለዋል።


 

በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ በጽናት በማለፍና በትጋት በመስራት ለስኬት የበቃው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለዚህ በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑንም አንስተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የሀገር መከላከያ እና የፖሊስ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም