የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሌና የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኮን ሚቾል አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሌና የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኮን ሚቾል አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፦የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊና የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኮን ሚቾል በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ።
ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተመሳሰይ የግሪናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዲኮን ሚችል የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ተቀብለዋቸዋል።
ጉባኤው በአፍሪካ እና በካሪቢያን አገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቴክኒክ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው።