ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግብጽ አቻው ተሸነፈ 

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ  ብሄራዊ ቡድን በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብጽ ጋር ባደረገው የምድብ አንድ ሰባተኛ ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ሳላህ እና ኦማር ማርሙሽ በፍጹም ቅጣት ምት ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በስድስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የምድቡ መሪ ግብጽ ነጥቧን ወደ 19 ከፍ አድርጋለች።

ኢትዮጵያ ቀጣይ የምድብ ጨዋታዋን ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከሴራሊዮን ጋር በላይቤሪያ ሞኖሮቪያ ታደርጋለች።

ግብጽ ከቡርኪናፋሶ ጋር ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም ትጫወታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም