ቀጥታ፡

ቻለው ለሜቻ  ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ቡድኑ ከኬንያ ጋር ላለበት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ለ33 ተጫዋቾች የመጀመሪያ ዙር ጥሪ አድርገዋል። 

ብሔራዊ ቡድኑ በፖላንድ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 ለሚካሄደው 12ኛው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር መስከረም 11 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም ላይ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳፍ ፌዴሬሽን ባለፈው ሳምንት ቻለው ለሜቻን የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ይታወቃል።

ዋና አሰልጣኙ ለጨዋታዎቹ ዝግጅት ዛሬ ለ33 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። 


 

አበባየሁ ጣሰው (መቻል)፣ አበባ አጄቦ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) እና ሮማን አምባዬ (ሸገር ከተማ) ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ናቸው። 

በተከላካይ መስመር ፍቅረአዲስ ገዛኸኝ (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ለምለም አስታጥቄ (ሃዋሳ ከተማ)፣ መሰረት ማሞ (መቻል)፣ ሰናይት ሸጎ (መቻል)፣ መሰረት ወርቅነህ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ትዕግስት አዳነ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ባዩሽ ኪምባ (ሲዳማ ቡና)፣ ካምላክነሽ ሃንኮ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ቃልኪዳን ሸዋነህ (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ፀግነሽ አዴ (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ እና  ሂሩት ተስፋዬ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ስብስብ ውስጥ ተካተዋል። 

ቤተልሄም ተስፋዬ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤተልሄም መንተሎ (መቻል)፣ ቤዛዊት ንጉሴ (መቻል)፣  ሚሊየን ጋይም (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ሜላት አሊሙዝ (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ብርሃን ኃይለስላሴ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) እና ቅድስት ኬካ (ሃዋሳ ከተማ) የአማካይ ተጫዋቾች ናቸው። 

በአጥቂ መስመር እሙሽ ዳንኤል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዳግማዊት ሰለሞን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ታሪክ ጴጥሮስ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ምትኬ ብርሃኑ (ሲዳማ ቡና)፣ ማህሌት ምትኩ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ህድአት ካሱ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ትዕግስት ወርቄ (መቻል)፣ ሰላማዊት ጎሳዬ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ አይናለም አለማየሁ (ሸገር ከተማ) እና ሰናይት ኡራጎ (ሸገር ከተማ) ብሄራዊ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ደርሷቸዋል። 

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል። 

በፖላንድ አስተናጋጅነት እ.አ.አ በ2026 ለሚካሄደው 12ኛው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ።

አፍሪካ በውድድሩ ላይ አራት ሀገራት የማሳተፍ ኮታ ያገኘች ሲሆን ሀገራት በአራት ዙር የማጣሪያ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም