በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰናይት ኡራጎ በጨዋታ እና ህይወት ረጉ በፍጹም ቅጣት የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል።
በተያያዘም የድሬዳዋ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ በዝናብ ምክንያት 55ኛው ደቂቃ ላይ ተቋርጧል።
ጨዋታው ከተቋረጠበት ጀምሮ ነገ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ድሬዳዋ ከተማ በፊርማዬ ከበደ ሁለት ግቦች እና በፍሬነሽ ዮሐንስ ቀሪ ጎል 3 ለ 0 እየመራ ነበር።