ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድል ሲቀናው ይርጋጨፌ ቡና እና ልደታ ክፍለ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2017(ኢዜአ)፦ የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ በአበበ በቂላ ስታዲየም በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል።

ቦሌ ክፍለ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።


 

ሚሊዮን ጋይም እና ቤቲ ዘውዱ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

በሌላኛው መርሃ ግብር አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና ከልደታ ክፍለ ከተማ ያደረጉ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።


 

የሊጉ የሁለተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም