ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በራዮን ስፖርትስ ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በራዮን ስፖርትስ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2017(ኢዜአ)፦ በ2025/26 የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ዞን ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሩዋንዳው ራዮን ስፖርትስ 2 ለ 1 አሸንፏል።
በንያዮ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦዴቴ ንጉዌማ እና ስኮላስቲክ ጊኩንዲሮ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ረድኤት ማቲያስ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥራለች።
የወቅቱ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ከብሩንዲው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ ጋር መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ያደርጋል።
ኢትዮጵያን በሴካፋ ዞን ወክሎ በማጣሪያ ውድድሩ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በምድብ ሁለት ከብሩንዲው ቶፕ ገርልስ አካዳሚ እና ከሩዋንዳው ራዮን ስፖርትስ መደልደሉ ይታወቃል።
ዛሬ በኬንያ አስተናጋጅነት የተጀመረው የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
በውድድሩ ላይ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
ማጣሪያው የሚያሸነፍ ክለብ ሴካፋን ወክሎ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ይሳተፋል።