1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29/ 2017 (ኢዜአ)፦1 ሺህ 500ኛው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል /መውሊድ/ በአንዋር መስጂድ እየተከበረ ነው።
በበአሉ ላይ የእምነቱ ተከታዮች በማለዳ በአንዋር መስጂድ በመገኘት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስርአቶች በአሉን እያከበሩ ነው።
በታላቁ አንዋር መስጂድ እየተከበረ ባለው በአል የመጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የእምነቱ ተከታዮች፣ዑለማዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።