ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብጽ ጋር ላለበት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ካይሮ ገብቷል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 28/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብጽ አቻው ጋር ጨዋታውን ለማድረግ ካይሮ መድረሱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

23ኛው የፊፋ እ.አ.አ በ2026 በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጣምራ አዘጋጅነት ይደረጋል።

ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከግብጽ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሴራሊዮን፣ ጊኒ ቢሳው እና ጅቡቲ ጋር ተደልድላ እስከ አሁን ስድስት ጨዋታዎችን አድርጋለች።


 

ብሄራዊ ቡድኑ የምድብ ሰባተኛ ጨዋታውን የፊታችን አርብ ከግብጽ ጋር ያከናውናል።

ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ ካይሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሱን ኢዜአ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዋልያዎቹ በማጣሪያው ስምንተኛ ጨዋታቸውን ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከሴራሊዮን ጋር ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም