በባሌ ዞን የወባ በሽታን ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው

ሮቤ፤ ነሐሴ 27/2017(ኢዜአ):-በባሌ ዞን የወባ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል  የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ  መሆኑን  የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ሰይፉዲን መሐመድ እንደገለጹት በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች የወባ በሽታ ስርጭትን አስቀድሞ ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው ።

በአካባቢዎቹ በህዝብ ተሳትፎ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ስፍራዎችን  የማፋሰስና የማጽዳት ስራ  እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።


 

በተለይ የበርበሬ፣ ሀረና፣ ጉረዳሞሌን ጨምሮ ሌሎች ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰባት ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥቶ የመከላከሉ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከአካባቢው ጽዳት ጎን ለጎን ለ150ሺህ ሰዎች በበሽታው መከላከያ መንገዶች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማሳደጊያ ትምህርት መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡


 

በዞኑ እየተከናወነ ባለው የወባ በሽታ ቅድመ መከላከል ስራዎች ከ161 ሺህ በላይ የአርብቶ አደር ቤተሰብ አባላትን ከበሽታ ለመታደግ መታቀዱን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም