አይችሉም የተባልንበትን ምዕራፍ ዘግተናል-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
አይችሉም የተባልንበትን ምዕራፍ ዘግተናል-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 27/2017 (ኢዜአ)፡-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) በብዙዎች ዘንድ አይችሉም የተባልንበትን ምዕራፍ ዘግተናል ሲሉ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ በታዳሽ ኃይል ግንባታ ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ ከ13 ጊዜ በላይ በጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ ተደርገን ነበር ብለዋል።
ኢትዮጵያ ግን ሁሉንም ተግዳሮቶች በድል ተወጥታለች ብለዋል በመግለጫቸው።
ከሰማይ በታች ሥራውን ለማስቆም የተቆፈረውን ጉድጓድ ሁሉ በአመራር ጥበብና ብልሃት እንዲሁም በሕዝባችን የተደራጀ አቅም በመታገዝ ማለፍ ችለናል በማለት ተናግረዋል።
ግዙፉን የአፍሪካ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በደማችን፣በላባችን እና በአንጡራ ሃብታችን የሕዳሴ ግድባችንን ከነበረበት ቅርቃር በማውጣት አጠናቀነዋል ሲሉም ገልጸዋል።