2017 ዓ.ም ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪ ድሎች የተመዘገቡበት ነበር-ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
2017 ዓ.ም ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪ ድሎች የተመዘገቡበት ነበር-ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 27/2017 (ኢዜአ)፡- 2017 የበጀት ዓመት ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እመርታዊ ድሎች የተመዘገቡበት እንደነበር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ፤ የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለኢትዮጵያ በእጅጉ ስኬታማ ዓመት መሆኑን አስታውቀዋል።
ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አክለውም፥ 2017 የበጀት ዓመት ውስብስብ ፈተናዎችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እመርታዊ ድሎች የተመዘገቡበት ነበር ብለዋል።
ድሎቹ ብዙ ሊነገርላቸው የሚገባ፣ትምህርትም የሚቀሰምባቸው እንዲሁም ለቀጣይ ሀገራዊ ድሎች እንደወረት የሚወሰዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
መጪው አዲስ ዓመትም እነዚህን ድሎች በይበልጥ የምናሰፋበት ብሎም ተግዳሮቶቻችንን የምንቀንስበት እንዲሆን ሰፊ ዕቅድ ተቀምጧል ሲሉ አመላክተዋል።
ይህን መሠረት በማድረግም ወደ ንቅናቄ መገባቱን ነው የተናገሩት።
የጳጉሜን ወር ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርበት ድልድይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ቀናቱ በተለይም ለኢትዮጵያውያን በእጅጉ ልዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በቀጣዮቹ የጳጉሜን ቀናት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተናበበ አካሄድ እንደሚከበሩም ጠቁመዋል።